Loading
Loading
Loading
Loading
Loading
Loading
June 1, 2024
Chicago, IL

Aden Beshire

and

Biruk Asrat

June 1, 2024

Chicago, IL

Details

“አድርገህልኛልና፡ለዘለዓለም፡አመሰግንሃለው።” መዝ፦፶፩፣፱ የማክበር፡ሰላምታችንን፡እያቀረብን፣ የልጆቻችን፡ የአቶ፡ቡሩክ፡አሥራት፡ እና፡ የወ/ት፡ኤደን፡በሽር፡ የጋብቻ፡ሥነ፡ሥርዓት፡እንደ፡እግዚአብሔር፡ፈቃድ፡በቅዳሜ፡ዕለት፡ግንቦት፡፳፬፡ቀን፡፳፻፲፮፡ዓ/ም፡በችካጎ፡አቅራቢያ፣በዊተን፡ከተማ፡ውስጥ፡በሚገኘው፡በደብረ፡ምሕረት፡ቅዱስ፡ሚካኤል፡የኢትዮጵያ፡ኦርቶዶክስ፡ተዋሕዶ፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ይፈጸማል፤ከቅዳሴ፡በኋላም፣በኢትዮጵያ፡አቆጣጠር፡ከቀኑ፡፯፡ሰዓት፡ጀምሮ፡በቤተ፡ክርስቲያኑ፡አቅራቢያ፡በሚገኘው፡የሙሽራ፡መቀበያ፡አዳራሽ፡ውስጥ፡በመገኘት፡የምሳ፡ግብዣችን፡ላይ፡የደስታችን፡ተካፋይ፡እንዲሆኑልን፡በማክበር፡ጠርተንዎታል።ስለዕለቱ፡ጥሪ፡የበለጠ፡መረጃ፣የስልክዎን፡መነጽር፡በመጠቀምና፡ከታች፡የተቀመጠውን፡የፈጥኖ፡መላሽ፡ጠቋሚ፡ምልክት፡ተሳሳቢነት፡በመከትል፣በአዘጋጀነውን፡የአንድነት፡መርሐ፡ግብር፡ላይ፡ታዳሚ፡እንደሚሆኑልን፡ደስታዎን፡እንዲጋሩን፡እንጋብዞታለን። በኵረ፡ትጉሃን፡ቀሲስ፡አሥራት፡እጅጉ፡እና፡ ወ/ሮ፡ብርሃኔ፡ኃይሉ፣ አቶ፡በሽር፡የሱፍ፡እና፡ ወ/ሮ፡እጅጋየሁ፡ጌታቸው። “ቤትና፡ባለጠግነት፡ከአባቶች፡ዘንድ፡ይወረሳል፤አስተዋይ፡ሚስት፡ግን፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ናት።” ምሳሌ፦፲፱፣፲፬